ጉዱ ካሳ

Sem G.
2 min readJan 21, 2021

--

አንድ ህብረተሰብ መለወጥ ካለብን ከመንጋ አስተሳሰብ የተላቀቁ ፤ ከእኛ ተቃራኒ የሚቆሙ፣ከባዱን መንገድ የሚመርጡ ተሟጋቾች ያስፈልጉናል።ለዚህ ምሳሌያችን የፍቅር እስካመቃብሩ ጉዱ ካሳ ነው። ህብረተሰቡ ተቀብሎ የኖረውን የፊውዳል ስርአት የተሟገተ ተራማጅ፣ የአይምሮ ጤና እንዳጣ ሰው የሚታይ ሽቅብ ተጓዥ ድንቅ ሰው ነው ።ይህ ሰው በዚህ ዘመን ቢኖር የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ እንደሚኖረው እርግጠኛ አይደለሁም።ቢኖረው እንኳን የስድብ አስተያየት የእለት ቀለቡ ይሆን ነበር።

የዘመናችን ተሟጋቾች — activists — ከጉዱ ካሳ የሚለዮት ህዝበኛ በመሆናቸው ነዉ።ሲጀመር መታገያቸው። ህዝብን በቀላሉ ማሰባሰቢያ የሆነው ብሔርን መሰረት ያደረገ ነዉ።ይህ ስርአት — order — ያፈርስ ይሆናል እንጂ ለመገንባት አይችልም።

የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ሆነ እና ነገሩ ከነበረው አስከፊ ስርአት የተነሳ በየትኛውም አካሄድ ለውጥ መምጣቱን እንጂ ለውጥ ሲመጣ ከለውጡ በኍላ የሚያመጣውን ጦስ ማንም የተመለከተዉ የለም።
ይህ የጥቂቶች በስልጣን የመቆየት ጥማት እና የነዋይ ስግብግብነት መገለጫው የነበረውን ስርአት የብሄር የበላይነት እና ጭቆና ጋር ያያያዘ ነበር።ከመሬታቸው የተፈናቀሉ ገበሬዎች ብሄራቸው ምን ይሁን ምን ከተቀራማቾች ዕይን እንደማያመልጡ ሳያስተዋል የጭቆና ስርአት ግብኣት አድርጎ ተጠቀመባቸው።

በዚህ መንገድ ሄደን ውጤቱ መጥቷል የሚል ሙግት ይነሳ ይሆናል።ነገር ግን ይህ ውጤት ዘላቂ የሃገር ግንባታን ያረጋግጥልናል ወይ ነው ጥያቄው።የሃገር ግንባታ የጠንካራ ተቋማት ድምር ውጤት ነው።

ችግሩን ከዲሞክራሳዊ ስርአት መታጣት ወደ ብሄር ጭቆና ቀይሮ የታገለ ማህበረሰብ ከለውጡ መለስ የብሄር ጥቅም ይገባናል የሚል አስተሳሰብን መተካቱ ተፈጥሮአዊ ሂደት ነው።በዚህ ውስጥ የተሟጋቾች — activists — ሚና ከፍተኛ ነው። መርህ አልባ የራስን ብሄር ጥቅም ማስከብር እና ከህዝብ ፍላጎት ጋር አብሮ መፍሰስ በሚያስገኘው ጊዚያዊ ጭብጨባ ላይ ተመስርቶ መንቀሳቀስ የነዚህ ተሟጋቾች መገለጫ ነው ።

ከተራ ጊዜያዊ ተወዳጅነት ይልቅ በህዝቡ ውስጥ ያለውን ኢዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እንዲሁም አላስፈላጊ ጥላቻ የሚሞግት ፣ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር በፍቅር እና በአንድነት መቆምን የሚሰብክ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ ሃገራችን ትፈልጋለች።

ሁሉም አካባቢውን ቢያጸዳ ሃገር ትፀዳለች እንዲሉ እዛኛው ሰፈር ላይ ከመጠቆም በአጠገባችን ያለውን መጥረጊያችን የሚደርስብትን ሰፈር (Circle of influence ) አብሮ የማያኖር ፣ለእኔ ብቻ የሚል እኩይ አስተሳሰብ እናፅዳ።

መፅሃፉም በምሳሌ ላይ ከሚያቆላምጥ ይልቅ የሚገስፅ ቆይቶ ሞገስ ያገኛል አይደል የሚለው ?

Sign up to discover human stories that deepen your understanding of the world.

Free

Distraction-free reading. No ads.

Organize your knowledge with lists and highlights.

Tell your story. Find your audience.

Membership

Read member-only stories

Support writers you read most

Earn money for your writing

Listen to audio narrations

Read offline with the Medium app

--

--

Sem G.
Sem G.

Written by Sem G.

Media and Software professional sharing life lessons, random ideas and insights. Slow is smooth, smooth is fast.

No responses yet

Write a response